አዲስ አበባ ፤ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት ። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት የፌደራል ከተማነትን ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በ1999 አ.ም በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ወደ 2,739,551 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ናት።
ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍልውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን ወደ አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ነች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር። በዓለም ዙሪያ ካሉ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች በዘረመል መረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናት የሰው ዘር ከአዲስ አበባ ቅርብ ከሆነ ቦታ ከ100,000 ዓመታት በፊት እንደተበተነ ያመለክታል። አዲስ አበባ፦ በ ShapeMiles ላይ የሩጫ መንገዶችን ማሰስ፣ ርቀትንና ዳገትን ማወዳደር እንዲሁም ልምምድዎን ከአየር ሁኔታ ጋር ማቀናጀት ይችላሉ።
Population: የከተማው ነዋሪ፦ 3.86 ሚ